Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የአፍሪካ የምግብ ሽልማት አዲስ ሊቀ-መንበር ሾሟል

February 18, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የዜጎችን መፃኢ ዕድል ለመወሰን መሪዎች ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል

በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የዜጎችን መፃኢ ዕድል ለመወሰን መሪዎች ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ የኢፌዴሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ) የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ) ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና እና የምጣኔ-ሀብት ዕድል በር ለከፈቱ ግለሰቦች እና ተቋማት የሚሰጠው “የአፍሪካ የምግብ ሽልማት” አዲስ ሊቀ-መንበር ሾሟል።

የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና የሽልማቱ ኮሚቴ የቀድሞ ሊቀ-መንበር ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለአዲሱ “የአፍሪካ የምግብ ሽልማት” ሊቀመንበር የቀድሞው የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ጃካያ ሚሪሾ ኪኪዌቴ ኃላፊነቱን አስረክበዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ) የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የግብርና ሽግግር ቀጣይነት ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በአፍሪካ አንገብጋቢ የሆነውን የምግብ ዋስትናን እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑን በመግለጽ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ሀገራት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በተለይ በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የዜጎችን መፃኢ ዕድል ለመወሰን መሪዎች ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና የሽልማቱ ኮሚቴ የቀድሞ ሊቀ-መንበር ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በበኩላቸው፥ ሽልማቱ የአፍሪካን ግብርና ለማዘመን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት እገዛ ይኖረዋል ብለዋል።
ሽልማቱ በአህጉሪቱ በግብርና እና ምግብ ዋስትና አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦች እና ተቋማት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ እና ልምድ ልውውጥ ለአህጉሪቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።
አዲሱ “የአፍሪካ የምግብ ሽልማት” ሊቀመንበር የቀድሞው የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ጃካያ ሚሪሾ፣ በተሰጣቸው ኃላፊነት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ የአፍሪካን ግብርና እና የምግብ ዋስትና ለማሻሻል እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የአፍሪካ የምግብ ሽልማትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።
በአፍሪካ የምግብ ሽልማት ውስጥ ካሉት ኮሚቴዎች መካከል የቀድሞ የኢሴክስ መሥራች ዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን ይገኙበታል።
“የአፍሪካ የምግብ ሽልማት” የአፍሪካን ግብርና ለሚያሸጋግሩ ግለሰቦች እና ተቋማት 100 ሺህ ዶላር የሚሸልም መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት
ShareTweetShare
Previous Post

የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች የጉባዔ ነገ ይጀምራል

Next Post

36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post

36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል

በአውስትራሊያ የዓለም ሀገር አቋራጭ ውድድር

ለአፍሪካዊ ችግሮቻችን አፍሪካዊ መፍትሄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?