
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋቂ መሃመት በአህጉሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች እና መጻኢ እጣ ፈንታ ዙሪያ እየተካሄደ በሚገኘው 36ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ መክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ ንግግር አድረገዋል።
ሙሳ ፋቂ በንግግራቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጥን አፍሪካን በተለያዩ መልኮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ትወዳዳሪ እና ተሳታፊ ያደርጋታል ብለዋል።
ይህ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እውን እንዲሆን መሪዎች በግምባር ቀደምትነት ሃላፊነቱን በመውሰድ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ሊቀመንበሩ አያይዘውም በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ችግሮች መካከል አንዱ በፖለቲካ እና በፀጥታ መስክ ላይ ነው ያሉ ሲሆን ይህም ሽብርተኝነት አካባቢያዊ ግጭቶች ታክለውበት አህጉሪቱን መፈተኑን ጠቅሰዋል።
በአህጉሪቱ የተለያዩ ሃገራት ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ስልጣን በያዙ አካላት ላይ ማዕቀቦች መጣላቸውንም አስታውሰው ማዕቀቡ የታስበውን ውጤት አላመጣም ነው ያሉት።ይልቁንም ማዕቀቦቹ ህዝቡን መጉዳታቸውን ገልጸው ከዚህ በመነሳት በቀጣይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ መሰራት አለበት ብለዋል።
በቀጣይም አህጉሪቱን በታለመለት የእድገት ጎዳና ለማራመድ ግጭት የመፍታት እና ቀድሞ የመከላከል ፕሮጀክቶች በስፋት ሊሰራባቸው እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ አስገንዝበዋል።
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









