፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 09 2016| NBC ETHIOPIA-በሩዋንዳ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት ሰው ለአራተኛ ጊዜ ማሸነፋቸው ተነግሯል፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2000 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጣን የያዙት የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለአራተኛ ጊዜ በተካሄደው ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ መራጮችን ድምፅ ማግኘታቸውንና የስልጣን መደላድላቸውን ማረጋገጣቸውን ነው የተሰማው፡፡

የሩዋንዳው የምርጫ ኮሚሽነር ካጋንጋሞ በሩዋንዳ ፕሬዝዳንታዎ ምርጫ የካጋሜን አሸናፊነት በይፋ አውጀዋል፡፡ የስልሳ ስድስት አመቱ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ሲሆኑ ባለፈው ሰኞ በተካሄደው ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን የአናዶሉ ዘገባ ያስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












