Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Technology

የዓለም የምንግዜም አደገኛ የሳይበር ጥቃቶች

May 28, 2024
in Technology
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 20 2016| NBC ETHIOPIA- ለዓለም ደህንነት ትልቅ የራስ ምታት ከሆኑት መካከል የሚጠቀሰው የሳይበር ጥቃት በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶችን ሲያስከትል ሰንብቷል፣ እያስከተለም ይገኛል፣ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ይጠበቃል፡፡

መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው Pentest People የተሰኘው ድህረገጽ ዓለም እስከዛሬ ካስተናገደቻቸው የሳይበር ጥቃቶች በአደጋኛነታቸው ከአንድ እስከ አምስት ያስቀመጣቸውን እንመልከት፡፡ 

በጎርሮሳውያኑ ግንቦት 2017 በአብዛኛው የዓለም ክፍል በሚገኙ የንግድና የተለያዩ ተቋማት ላይ የደረሰው የሳይበር ጥቃት በዓለማችን ከደረሱ እጅግ አደገኛ አምስት የሳይበር ጥቃቶች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ “The WannaCry Ransomware Attack” በሚል የሚታወቀው ጥቃቱበ150 ሀገራትበሚገኙ ከ200 ሺህ በላይ ኮምፒውተሮች ላይ የተቃጣ ነበር፡፡

ጥቃቱ በአይነቱ ያልተለመደ ስለነበር በርካታ ድርጅቶች ለእንዲህ አይነቱ ጥቃት በጭራሽ ዝግጁ አልነበሩም፡፡ ከአንዱ ኮምፒውተር ወደሌላኛው ኮምፒውተር በቀላሉ የሚሰራጭ በመሆኑም በፍጥነት ለመዳረስ ጊዜ አልፈጀበትም ነበር፡፡ እንደ እድል ሆኖ አንድ የደህንነት ተመራማሪ ስርጭቱን የሚገታ መፍትሄ በማግኘቱ ከበለጠ ውድመት ዓለምን ማትረፍ ተችሏል፡፡ በጥቃቱ የደረሰውን ውድመት ማከም ግን አልተቻለም፡፡

በአደገኛነቱ የሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የNotPetya ቫይረስ ነው። ሰኔ 2017 ያጋጠመው ቫይረሱ በፍጥነት ነበር በመላው ዓለም የተሰራጨው፡፡

ቫይረሱ ሰዎችን በማታለል ኮምፒውተሮቻቸውን ለብሽት የሚዳርግና ያለፍቃዳቸው ኮምፒውተራቸውን ሌሎች እንዲጠቀሙት የሚያደርግ ሶፍትዌር ኮምፒውተሮቻቸው ላይ እንዲጭኑ የሚያደርግ ነበር፡፡

NotPetya ቫይረስ ያላጠቃው የንግድ አይነት እንደሌለ ይነገርለታል፡፡ ቫይረሱ መጀመሪያ ላይ በዩክሬን በተለመደ አንድ የሂሳብ ሶፍትዌር አማካኝነት በመሰራጨቱ በተለይ የዩክሬን ድርጅቶች ክፉኛ ተጠቅተዋል፡፡ በመቀጠል በመላው ዓለም የተዳረሰው ቫይረሱ ያስከተለው የሳይበር ጥቃት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል፡፡

ኮምፒውተሮቻቸው በቫይረሱ የተጠቃባቸው ሰዎች ኮምፒውተሮቻቸው ላይ ያሉ መረጃዎችን እንዳያገኙ አድርጓቸዋል፡፡ በእዚህ ሳቢያ በርካታ የንግድ ድርጅቶች ለመዘጋት ተገደዋል። በጥቃቱ መረጃዎቻቸው የጠፋባቸው ግለሰቦች መልሰው መረጃቸውን ማግኘት አለመቻላቸው የNotPetya ቫይረስ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል፡፡

ስለጥቃቱ ዓላማ ግን እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም፡፡ አንዳንዶች በመረጃ ጦርነት ሳቢያ የተፈጠረ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ አላማውን በሳተ ቀልድ የተፈጠረ ነው ባይ ናቸው፡፡

የNotPetya ቫይረስ አለምን ባስጨነቀበት አመት የተከሰተው የEquifax Data Breach ሌላኛው የዓመቱ ድርብ ፈተና ነበር፡፡

የሳይበር ጥቃቱ የደረሰው በአሜሪካ ሸማቾች እና ንግዶች፣ የንግድ ማንነት እና የማጭበርበር መፍትሄዎች የፋይናንስ ግብይት እንዲሁም የትንታኔ አገልግሎቶችን የሚሰጠው Equifax ኤጀንሲ ላይ ነበር፡፡

147.9 ሚሊዮን አሜሪካውያን፣ ከ 15 ሚሊዮን በላይ የእንግሊዝ ዜጎች እና ወደ 19 ሺህ የሚጠጉ የካናዳ ዜጐችን የግል መዛግብት ለምዝበራ የዳረገው ጥቃቱ ከማንነት ስርቆት ጋር በተገናኘ በታሪክ ከታዩት ግዙፍ የሳይበር ወንጀሎች አንዱ ያደርገዋል።

ጠላፊዎቹ እንደ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሮች፣ የዜጎችን የውልደት ቀን እና አድራሻዎች የመሳሰሉ ወሳኝ መረጃዎችን ማግኘት ችለዋል። ይህም በቢዝነስ ተቋማትና ደንበኞቻቸው ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን አስከትሏል፡፡ ይህ ጥቃት ድርጅቶች የደህንነት ስርዓታቸውን እንዲያጠብቁ ማንቂያ እንደሆናቸው ይነገራል፡፡

በአደገኛነቱ በአራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የጥቅምት 2016ቱ የMirai Botnet Attack ነው፡፡

ከበይነ መረብ ጋር የተገናኙ መገልገያዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲሆን በድህረ-ገጾችና ንግዶች ላይ የተቃጣ ነበር፡፡

ጥቃት አድራሾቹ ጥቃቱን የሰነዘሩት በተበላሹ መሳሪያዎች አማካኝነት ሲሆን ተጠቃሚዎች ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እንዳያገኙ አድርጓል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ጥቃት አድራሾቹ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው ሊያደርጉት ይችላሉ ማለት ነው፡፡ የMirai botnet ጥቃት ተጽዕኖው ዛሬም ድረስ እንዳልጠፋ የሚነገር ሲሆን ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ መሳሪያዎች ለሳይበር ጥቃት ምን ያህል ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ እንዲሁም የሳይበር ጥቃት አጥፊነትን አሳይቷል። በስተመጨረሻ ጥቃቱን መግታት የተቻለ ሲሆን ጥቃት አድራሾቹ በቁጥጥር ስር ውለው ወህኒ ተወርውረዋል፡፡

በአምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው በጎርጎሮሳውያኑ 2014 የደረሰው የያሁ የሳይበር ጥቃት ነው፡፡ 500 ሚሊዮን አካውንቶች ላይ ያነጣጠረው ጥቃቱ መዘዙ ከሶስት ቢሊዮን ለሚልቁ የያሁ ተጠቃሚዎች ተርፏል፡፡

የተጠቃሚዎችን ስም፣ የልደት ቀን፣ አድራሻ እና ማለፊያ ቁጥር ያሉ መሰረታዊ ግላዊ መረጃዎች በጥቃት አድራሾቹ እጅ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ በበይነ መረቡና በደንበኞቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አድርሷል፡፡ የያሁ የሳይበር ጥቃት በድርጅቱ ታሪክ ትልቁ የመረጃ ጥሰት ሲሆን ያደረሰው ጉዳት መጠነ ሰፊ ነበር፡፡

ሰርጎ ገቦቹ ጥቃቱን ያደረሱት በቀላሉ እንደነበር ኤፍ.ቢ.አይ በ2016 ይፋ ባደረገው መረጃ አስታውቋል፡፡ ይህን የታዘቡ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች በሁሉም መስክ ያሉ የደህንነት ሰራተኞች በቂ የደህንነት ስልጠናዎችን ሊወስዱ ይገባል ሲሉ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ 2023 ዓለም በሳይበር ጥቃት ሳቢያ በዓመት ስምንት ትሪሊዮን ዶላር እንድታጣ እንዳደረጋት አለም አቀፍ የሳይበር ኢኮኖሚን እና የሳይበር ደህንነት እውነታዎች፣ አሀዞች ላይ የሚሰራው ሳይበር ሴኪዩሪቲ ቬንቸርስ የተሰኘው ኩባንያ መረጃ ያሳያል፡፡ በተያዘው ዓመት ቁጥሩ ወደ 9.5 ትሪሊየን ዶላር ከፍ እንደሚል ኩባንያው ገልጿል፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

የራፋህ ጥቃት

Next Post

አጫጭር የሃገር ወስጥ መረጃዎች

Related Posts

ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር
News

ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር

October 8, 2026
23
⁨የ AI ተስፋ እና ስጋት | የጋዜጠኛው ህልውና እና AI | የኤዲተሮች ጠረጴዛ | ​
Technology

⁨የ AI ተስፋ እና ስጋት | የጋዜጠኛው ህልውና እና AI | የኤዲተሮች ጠረጴዛ | ​

September 30, 2026
15
የመምህር ረዳት AI መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ ማዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
Education

የመምህር ረዳት AI መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ ማዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

June 5, 2026
29
ለኒውክሊየር ኃይል ጣቢያ ግንባታ የሚሆን ምቹ አካባቢን በጥናት የመለየት ሥራ ተጀምሯል
News

ለኒውክሊየር ኃይል ጣቢያ ግንባታ የሚሆን ምቹ አካባቢን በጥናት የመለየት ሥራ ተጀምሯል

May 18, 2026
38
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መግለጫ
Technology

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መግለጫ

April 4, 2026
79
የሳይበር ማጭበርበሮችን እንዴት እንከላከል? _ዘመን እና ቴክኖሎጂ
Technology

የሳይበር ማጭበርበሮችን እንዴት እንከላከል? _ዘመን እና ቴክኖሎጂ

February 23, 2026
12
Next Post
አጫጭር የሃገር ወስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሃገር ወስጥ መረጃዎች

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

የመጀመሪያው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ሀገርአቀፍ ኤግዚቢሽን

የመጀመሪያው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ሀገርአቀፍ ኤግዚቢሽን

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?