አዲስ አበባ | ጥር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA-የፌደራል የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት ሪፖርት በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ከ1 ነጥብ ሁለት ቢሊዮንብር በላይ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡


ኮሚሽኑ ሙስና ለመከላከል ከሚያከናዉናቸው ስራዎች መካከል አስቸኳይ የሙስና መከላከል አንዱ ሲሆን ሙስና ከተፈፀመ በኋላ ሳይሆን ጉዳዩ ጉዳት ሳይደርስ በሂደት ላይ መግታት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ኮሚሽኑ እንደ ሃገር በስድት ወራት ዉጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን እና የሃገር ንብረትን ከሙስና ምዝበራ ማዳን መቻሉ አንስቷል፡፡
ፀረ ሙስና ኮሚሽን በመግለጫው እንዳስታወቀው በሃገር አቀፍ በከተሞች ተቋማዊ እና መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የሙስና መከላከል ተግባር ለማከናወን የሚረዳ የጥናት ስራዎች መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ቢሆንም ሙስና ፈታኝ ሆኖ እንደቀጠለ ተነስቷል፡፡ በከፍተኛ መጠን ሙስናም ከሚተገበርባቸው ዘርፎች የመሬት አስተዳድር ግንባር ቀደም እንደሆን የተጠቆመ ሲሆን በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ነው ተብሏል፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












