አዲስ አበባ | ህዳር 05 2016| NBC ETHIOPIA -የ7 ዓመት ህፃን ልጁን በመደብደብ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረጉ ወላጅ አባት እና የእንጀራ እናት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጠራባቸው ይገኛል::

በእሱፈቃድ ታምራት የተባለው የ7 ዓመት ህፃን የተወለደው በእናቱ እና በወላጅ አባቱ መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ የፍቅር ግንኙነት ነበር፡፡
ወላጅ እናት ህፃኑን ከወለደች በኋላ ያለ ወላጅ አባቱ ድጋፍ እና እርዳታ ለ6 ዓመት ከወራት ያህል በብዙ ፈተና ውስጥ ሆና ብቻዋን እየኖረች አሳድጋዋለች ፤ነገር ግን ኑሮ እየከበዳት ሲመጣ ልጇም አብሯት እንዳይጎሳቆል በማሰብ ሃምሌ 18 ቀን 2015 ዓ/ም ለወላጅ አባቱ አስረክባ እሷ ወደ ጎዳና ኑሮ ወጣች፡፡
ይሁን እንጂ ህፃን በእሱፈቃድ ሌላ ሚስት አግብቶ ወደሚኖረው አባቱ የተሻለ ህይወት እንዲገጥመው ታስቦ ቢመጣም ነገሩ የሆነው የተገላቢጦሽ ነው፡፡
በወላጅ አባቱም ሆነ በእንጀራ እናቱ በየጊዜው ድብደባ ይደርስበታል፤ በብረት ሰንሰለት እየታሰረ መከራውን ያያል በደረሰበት ፤የስነ ልቦና ቀውስ ሰገራውን መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ እንኳ ድብደባው አልቀረለትም፡፡ድንገት የሚያመልጠውን ሰገራ እና ምግብ በልቶ በሆዱ አልረጋ ብሎት የሚያስመልሰውን በምላሱ እንዲልስ እስከማድረግ የደረሰ ግፍ ሲፈፀምበት ቆይቷል፡፡
በጥቅምት ወር 2016 ዓ/ም ህፃን በእሱፈቃድ በደረሰበት ድብደባ ራሱን ስቶ ሲወድቅ ወላጅ አባቱ እና የእንጀራ እናቱ አፋፍሰው ወደ ጤና ጣቢያ ይዘውት ይሄዳሉ፡፡
ጤና ጣቢያ የደረሱት ግን ህይወቱ ካለፈ በኋላ ነበር የህፃኑ መሞት በጤና ባለሙያዎቹ ሲነገራቸው አባቱ እና የእንጀራ እናቱ የአስክሬን ሳጥን ገዝተን እንምጣ ብለው በዚያው ቀርተዋል፡፡
ስለተፈፀመው ወንጀል አቤቱታ የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰው መግደል ወንጀል ምርመራ ክፍል ተጠርጣሪዎቹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ ይገኛል፡፡
የህፃን በእሱፈቃድ አስክሬን በጎረቤት እና በአካባቢው ነዋሪዎች ትብብር በቀጨኔ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በክብር እንዲያርፍ መደረጉን ከአዲስ አበባ ፖለስ በማህብራዊ ትስስር ገጽ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












