አዲስ አበባ | ጥቅምት 29 2016| NBC ETHIOPIA – ኢትዮ ቴሌኮም ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ የውሃና እና ኢነርጂ ሀብቶችንና መሰረተ ልማትቶችን ዘመናዊ ለማድረግ ብሎም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በጋራ ለመተግበር የሚያስችል ነው። በተጨማሪም ደንበኞች ወርሀዊ የውሃ ክፍያቸውን በቴሌ ብር መክፈል እንዲችሉ የሚያደርግ ነው።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በውሃ ሀብት ዘርፍ ላይ መረጃዎችን ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለማደረጀት እና በዘርፉ ለሚገኙ ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ ስምምነቱ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል። ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢዎችን በቀላሉ ለመፈፀም ብሎም በቀጣይ ለሚከናወኑ ድጋፎዎች ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በጋራ ስምምነቱ ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብ፣ የዲጂታል ሶሉሽኖስ መትከልና ማስፋፋት እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍና የአቅም ስልጠና መስጠትን ያካተተ ነው ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከ2አመት በፊት ለደንበኞቹ ያስተዋወቀው የቴሌ ብር ዲጂታል መተግበሪያ ከ35ሺ በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ከ7 ቢሊዮን በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተደርጎበታል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












