ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣ የሕወሓት እና የሻዕቢያን ጥምረት አውዳሚ እና አደጋው ከባድ እንደሚሆን አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው «ከነፃነቱ በፊት» የኤርትራ ከተሞች ያበቡና ያሸበረቁ ነበሩ፡፡ “ዛሬ ግን የመንደር ያህል ሆነዋል” ያሉ ሲሆን፣ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል በነበረችበት ወቅት ከአፍሪካ የኢንዱስትሪ ማእከል እንዲሁም ከ300 በላይ ፋብሪካዎች ባለቤት መሆኗን አስታወሰዋል፡፡
ሆኖም የሻዕቢያ አመራሮች ሀገሪቱን ከነበረችበት ወደ ከፋ የኢኮኖሚ ውድቀት እንደመሯት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒትሩ፣ አሑናዊው የኢርትራ ሁኔታ የዚሁ የጥፋት መንገዳቸውን ማሳያ ነው። አያይዘውም እንደ አስመራ፣ ምፅዋ እና ዓሰብ ያሉ ከተሞች ዛሬ የልማት ማዕከልነታቸውን አጥተው ሰው አልባ እና ከመደበኛ የኢትዮጵያ ከተሞች ያነሱ መሆናቸውን ገልጸው፣ የኤርትራ ህዝብ ከነፃነት በኋላ የነበረውን ሁሉ አጥቷልም ብለዋል።
ሻዕቢያ የሀገሩን ዕድገትና ተቋማትን መገንባት ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ጠላቶች መሳሪያ መሆኑ የተፈጥሮ አጎራባችነትን የሚያበላሽ ተግባር ነው ያሉት፡፡ ይህ የጥፋት ኃይሎቹ ጥምረት ቀጠናዊ ትስስርን የሚያናጋ እንዲሁም ለሻዕቢያ ጥይት የሚያቀበሉ የውጭ አካላት የራሳቸውን የውስጥ ቀውስ መፍታት ሳይችሉ ለሌላው ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጡ አይችሉም ብለዋል ።
ባለፉት 35 ዓመታት የታየው ቀጠናዊ ተሞክሮ እንደሚያረጋግጠው፣ ለዘላቂ ሕልውና የሚያዋጣው ብቸኛው መንገድ እውነተኛ ወዳጅነት እና መልካም ጉርብትና ብቻ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በፅኑ ያምናል ነው ያሉት።
መንግሥት ያቀረበውን ሰላማዊ ጥሪ ጆሮ ዳባ በማለት የቀደመውን የስህተት መንገድ ለሚደግሙ አካላት አደጋው እጅግ ከባድ እንድሚሆንና ኢትዮጵያ ድንበሯን ለማስጠበቅ ያላትን ፍጹም ወታደራዊ፣ ስልታዊና ዲፕሎማሲያዊ ዝግጁነትንም አረጋግጠዋል።
በ – በረከት አስረስ












