
ዛሬ የቄራ አልማዝዬ ስፖርት ሜዳ እና ሥልጠና ማዕከልን በዘመናዊ መልኩ መልሰን ገንብተን ለስፖርት ቤተሰቡና ለወጣቶቻችን ማበርከታችን ትልቅ ደስታ ነው።
ይህ ሜዳ በታሪኩ ለኢትዮጵያ ኩራት የሆኑ ታዋቂ ስፖርተኞችን አፍርቷል። ዛሬም ከዚህ ሜዳ አዳዲስ የስፖርት ጀግኖች፣ የሀገር ኩራቶችና የድል ባለቤቶች እንዲፈልቁ እድሉን እየፈጠርን ነው።

ሜዳው ከዚህ ቀደም በአቧራና በጥሻ ተውጦ፣ ለስፖርት እንቅስቃሴ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ቆይቶ ነበር። ዛሬ ግን በድጋሚ ለወጣቶቻችን፣ ለታዳጊዎችም አካታች ሆኖ ስለተገነባ የችሎታቸው መድረክና የሕልማቸው ተስፋ ሆኖ ተመልሷል።
በከተማችን የስፖርት መሠረተ ልማትን ማስፋታችን ለወጣቶችና ለታዳጊ ልጆች ጤናማ፣ ተስፋ የሞላበትና የስኬት መንገድ እየከፈትን መሆናችን ነው። ከዚህ ሜዳ በሀገርና በዓለም መድረክ የሚያበሩ ታላላቅ ስፖርተኞች ይፈልቃሉ የሚል እምነት አለን!
ይህ የጋራ ሀብታችን ነው። እንጠብቀው፣ እናልማበት፣ በጋራም እናሳድገው!
ለወጣቶቻችን ዕድል እንፍጠር፤ ለሕልማቸው መንገድ እንክፈት፤ ለኢትዮጵያም አዲስ የድል ታሪክ እንጻፍ












