
ኢትዮጵያ የጠላቶችን እኩይ ተግባር በብቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል።
አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር በምርጫው ለተሳተፉ 54 ሚሊዮን ዜጎች ምስጋና የቀረቡ ሲሆን በድምጻቸው ሀገር ለማጽናት ላደረጉትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተደረገ ተብሎ የሚታልፍ ብቻ ሳይሆን በብዙ መልኩ ትርጉም ያለው እንደሆነ ተናግረዋል።
ምርጫው በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ባህል እያደገ መምጣቱንየሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጠና ኢ- ተገማች እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው ለዚህም እስቀድሞ መዘጋጀት ከእዳ ይልቅ ምንዳን እንደሚያመጣ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በታሪክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጉዳዮች ዝግጁ ባለመሆኗ ብዙ ዋጋ መክፈሏን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ካለፉት ስህተቶቿ በመማር ለሚመጡባት የጠላቶችን እኩይ ተግባር እና ተግዳሮቶችን ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓን አመልክተዋል።












