
ናይጄሪያ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ በኋላ ለሰሜን ጎረቤቷ ኒጀር የኤሌክትሪክ አቅርቦት አቋርጣለች።
እርምጃው በኒጀር የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከጣሉት ማዕቀብ ጋር የተጣጣመ ነው ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች መዘገባቸውን አናዱሉ ገልጿል።
ኒጀር 70 በመቶውን የኤሌክትሪክ ኃይል ከናይጄሪያ ታገኝ እንደነበር ታውቋል ። ናይጄሪያ አባል የሆነችበት የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ECOWAS) መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎ በኒጀር ላይ ማዕቀብ ለመጣል ወስናለች ።
የኒጀር ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዙም ሀምሌ 26/2023 በፕሬዚዳንት ጥበቃ አባላት መያዛቸውን እና በዚያ ምሽት ወታደራዊ አመራሩ ስልጣን መያዙን አስታውቋል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












