
ከቦሌ ብራስ – ኤድናሞል – አትላስ እስከ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክርስቲያን ያለው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች እና ለሞተር ሳይክል መከልከሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
መንገዱ ለሚሠጠው የአገልግሎት ጥራትና ደህንነት ሲባል ከየካቲት 15 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ለከባድ ተሽከርካሪዎች (ከ2 ቶን በላይ ለሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ) እንዲሁም ለሞተር ሳይክል የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጾ፣ ክልከላውን በሚጥሱ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
ከቦሌ ብራስ – ኤድናሞል – አትላስ እስከ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክርስቲያን ያለው መንገድ እጅግ ባማረ ሁኔታ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
NBC ETHIOPIA












