Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Economy

የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ስለመደረጉ የተሰጠ መግለጫ

የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ስለመደረጉ የተሰጠ መግለጫ

February 11, 2026
in Economy, News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሟላ የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርም መደረግ ከጀመረበት ሀምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ፤ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማጎልበት የሚያስችሉ የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በአሁነ ወቅትም የውጭ ምንዛሪ ገበያን የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ በውጭ ምንዛሪ መመሪያ ላይ የሚከተሉትን ማሻሻያዎች ማድረጉን ያሳውቃል፡፡

1. የአገልግሎት ላኪዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ በሪቴንሽን ሂሳባቸው ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ተፈቅዷል፡፡

2. ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ የሚያገለግል ዓለምአቀፍ ካርድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

3. ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ያለው የባንክ ደንበኛ ሕጋዊ ሰነዱን ሂሳብ ለከፈተበት ባንክበማቅረብ፤ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቡን በመጠቀም ለትዳር አጋሩና ለልጆቹ የትምህርት፤የህክምናና የጉዞ ወጪ ክፍያ ማድረግ ይችላል፡፡

4. ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት የውጭ ምንዛሪ ምንጩ ከወጪ ንግድ የሚገኝን የውጭምንዛሪ ሳይጨምር በእርዳታ/ስጦታ አለያም ከሌላ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ የተንቀሳቃሽ፣ የቁጠባና የጊዜ ገደብ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላል፡፡

5. ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የውጭ ምንዛሪ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ይጠየቁት የነበረው አነስተኛ 100 የአሜሪካ ዶላር እንዲቀር ተደርጓል፡፡

6. ድርጅቶች የመዋእለ ነዋያቸውን ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያስመረመሩ ከሀገር ውጭበሌላ ሀገር መዋእለ ነዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

7. ማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ወደ ሀገር ይዞት የተመለሰውን የትኛውንም ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ያለ ጉምሩክ ሰነድ በባንኮችና ሕጋዊ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በኩል ወደ ብር መመንዘር አለያም ወደ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ በማስገባት ተቀማጭማድረግ ይችላል፡፡

8. ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ሰነድ ለባኮች በማቅረብ መጠነ- ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር ያልበለጠ የው ምንዛሪ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው እገዛ እንዲውል ከሀገር ወደ ውጭ ማስተላለፍ የሚችሉበት ሥርዓት ተፈቅዷል፡።

9. ባንኮች የፎርዋርድ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ ማካሄድ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

10. የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች፤ ኤምባሲዎችና በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ዓለምአቀፍ ተቋማት የተራድኦ ድርጅቶችን ጨምሮ ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ በባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡

11 ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያመጡት የውጭ ብድር (በገንዘብና በዓይነት) እና የሰፕላዬርብድርን የማጽደቅ ሥራ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መስፈርቶችን በተከተለ መልኩ ሙሉ በሙሉ በባንኮች እንዲከናወን ተፈቅዷል፡፡

12. ማንኛውም በወጪ ንግድ ላይ የተሰማራ ላኪ ድርጅት ከማንኛውም የውጭ አካል የቅድመ ክፍያ ስምምነት ላይ በመድረስ እና በሁለቱ ወገኖች የተደረሰውን የስምምነት ሰነድ ለላኪው ድርጅት ደንበኛ ባንክ በማቅረብ የቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላል።

13. በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለወደፊት የወጪ ንግድ ክፍያ እንደ ቅድመ ክፍያ የሚቆጠረው (ሀ) ስምምነቱ ገዥውን ለማመላከት ታስቦ “ቅድመ ክፍያው ለወደፊት ወጪ ወይም ገቢ ንግድ የሚውል” ወይ (ለ) ወደፊት ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦችን ከዘረዘረ ወይም የደረሰኝ ቁጥሩ ከተጠቀሰ አለያም የግብይት የውል ስምምነት ሰነድ ቁጥር በሚላከው የውጭ ምንዛሪ ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰ ይሆናል፡፡

14. ባንኮች ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ለግሉ ዘርፍ የውጭ ሀገር ብድር ዋስትና መስጠት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

15. ባንኮች የውጭ ተቋም በሚስጠው የማረጋገጫ ደብዳቤ እና ደንበኛው በሚያቀርበው ጥያቄ ላይበመመርኮዝ በአንድ ጉዳይ ከ20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከተመጣጣኝ የሌላ ሀገር ገንዘብ ያልበለጠ የውጭ ምንዛሪ ለህክምናና ለትምህርት ያለ ቪዛ እና የአውሮፕላን ትኬት ቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላሉ፡፡

16. ያለምንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን ሰነድ ለባንካቸው በማቅረብ እንዲሁም ባንኮች በመመሪያው መሰረት የቀረበው ሰነድ መሟላቱን በማረጋገጥ በትርፍ ክፍፍል መልክያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ማስወጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

17. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎችን የገንዘብ ፍሰትና ካፒታል የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የሚይዘውን ተቀማጭ ገንዘብ፣ (አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በሥራ ላይ ለሆኑ ቢሮዎች 30 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢያንስ ለስድስት ወራት በሥራ ላይ ላሉ ቢሮዎች 15 ሚሊዮን ብር) ተመላሽ ያደርጋል፡፡

18. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ቀደም ሲል ከነበረው የካፒታላቸው 10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ተሻሽሏል፡፡ ከዚህ በላይ የሆነ ትርፍ የውጭምንዛሪ ገንዘብ ለባንኮች መሸጥ አለበት፡፡

19. ሁሉም የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች አስፈላጊውን ሰነድ በመጠየቅ ለቪዛ፣ ለፓስፖርትና ለፈቃድ እድሳት ጥራ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ በቅርቡ ተሻሽሎ የወጣውን የባንኡን የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁጥር (FXD/04/2026) በድረ-ገጻችን nbe.gov.et ላይ ይመልከቱ፡፡

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: EthiopiaNational Bank of Ethiopia
ShareTweetShare
Previous Post

የየካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የእኩለ ቀን ዜናዎች

Next Post

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል

ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?