
በጋዛ በ2025 የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር 69 መድረሱን ሪፖርት አመላከተ፡፡
በ2025 በወጣ ሪፖርት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 111 ጋዜጠኞች እንደተገደሉ ተገልጿል፡፡
ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን በ2025 ባወጣው ሪፖርት 111 ጋዜጠኞች እንደተገደሉ ሲጠቅስ አምስት መቶ ያህሉ በእስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
ሕይወታቸው ካለፈ ጋዜጠኞች መካከል ስልሳ ዘጠኙ በጋዛ የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነትም አስር ጋዜጠኞች ሕይወታቸው አልፏል ብሏል ሪፖርቱ፡፡
ሪፖርቱን ያወጣው አይ ኤፍ ጄ በ2025 የጋዜጠኞች ሞት እንደጨመረ ገልጾ ዓለም ዓቀፍ ሕግ መጣሱ እና የፕሬስ ነጻነት እተከበረ አለመሆኑን አያይዞ ጠቅሷል፡፡
በአሕጉረ አፍሪካ በተለይም በሱዳን ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት የተነሳ ጋዜጠኞች ጥቃት እንደሚደርስባቸውም ዘገባው አመላክቷል፡፡
ሞዛምቢክ ሶማሊያ እና ዚምባብዌም ጋዜጠኞች የተገደሉባቸው ሀገራት መሆናቸውን የዘገበው አፍሪካን ኒውስ ነው፡፡
በ ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












