ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይናው ሺ ጂንፒንግ በታይዋን ላይ ዕርምጃ እንደማይወስዱ አረጋግጠውልኛል አሉ።
“እኔ በዋይት ሀውስ እያለሁ ታይዋን ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ቤይጂንግ አትፈጽምም “ያሉት ሪፐብሊካኑ “ያን ማድረግ የሚያመጣውን ጦስ ያውቁታልና “ሲሉ ምክንያያቸውንም አስቀምጠዋል። ምንም እንኳን ትራምፕና ሺ በቡሳን ደቡብ ኮሪያ ሲገናኙ የቴይፒን ጉዳይ ባይነጋገሩበትም ፕሬዚዳንቱ ታይዋን አትነካም ብለዋል።
ሺ ጂንፒንግ ስልጣን ላይ እያለሁ በታይዋን ላይ ጥቃት አይሰነዝሩም፣አረዳዳቸውም እንደዛ ነው በሚል ሀሳብ አጋርተዋል ሪፐብሊካኑ። ትራምፕ ፍላጎታቸውን ለሲ ቢ ኤስ 60 ሚነትስ ፕሮግራም ተናገሩ እንጂ የ ሺ አቋም ላይሆን ይችላልም ተብሏል ።
አሜሪካ በዴሞክራቶቹም ሆነ በሪፐብሊካኖቹ ታይዋንን የሚያዩበት የፖሊሲ መነጽር ” ሆነ ብሎ ስልታዊ ግራ ማጋባት”(strategic ambiguity) በመሆኑ ቻይናም በቀላሉ የትራምፕን አስተያየት አትመለከተው።
ቤይጂንግ ጦር ካዘመተች ታይዋንን እስከማገዝ የሚያደርስ የዋሽንግተን መርህ ነው። ፕሬዚዳንት ትራምፕም ቢሆኑ የሆነ ነገር ቢፈጠር ምላሹን እነ ሺ ይረዱታል ማለታቸው ይህኑ ያረጋግጣል።
ምስጢሬን ዝም ብዬ አልበትንም ያሉት ሪፐብሊካኑ በማር – ዓ-ላጎ ፍሎሪዳ መኖሪያቸው ”ያኛው አካል ይገባዋል ”በሚል አስገንዝበዋል። ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ቻይና በጉዳዩ ላይ ያለችው ነገር የለም።
ዘገባው የኤን ቢ ሲ ኒውስ እና ሲ ቢ ኤስ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












