18ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን የብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ተከበረ፡፡
የዘንድሮው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን ለኢትዮጵያ ማንሰራራት አዲስ ዘመን የድል ብስራት” በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኦሮምያ ቅርንጫፍ ተከብሯል።
የሰንደቅ አላማ ቀን ስናከብር ቀደምት ኢትዮጵያን በደምና በአጥንት መስዋእትነት ያቆያትን ኢትዮጵያ በማሳብ መሆን እንዳለበት ተገልጿል። ሰንደቅ አላማ የአነድነትና የማንነት መገለጫ በመሆኑ ትውልዱ የአባቶቹን አደራ በማስጠበቅ የኢትዮጵያን ሰላም ፤አንድነትና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
የዘንድሮው የሰንደቅ አላማ ቀን በመላው ኢትዮጵያውያን አንድነትና ትብብር እውን በሆነው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ማግስትመከበሩ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ የጀመረቸቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ በህዳሴ ግድብ የታየው አንድነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
በ -ሰላማዊት ወልደገሪማ












