የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ ውሏል።
የአፋር መሬቱም ሰውም ለሃገር ሉዓላዊነት ዋጋ የከፈለ ጀግና ሆኖ ብቻ አይጠቀስም፤ የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር ነው። የህዳሴ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ልማት ለሚተጋው ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ ይሆነዋል።
በድጋፍ ሰልፉም የተስተጋባው የአፋር ሕዝብ ድምጽ ለልማት እና ሰላም የወገነ፣ የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን ዕውን ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አይተናል፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












