የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን በማስመልከት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ሰልፎቹ ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል የደሴ ከተማ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል። የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸረቻትን ፀጋ በአግባቡ እንዳትጠቀም በተለያዩ መንገዶች ጫና ሲደረግባት መቆየቱን አንስተዋል።
ምክትል ከንቲባው አክለውም የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ወደ ወደብን ለማግኘት የምናደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው ብለዋል። ይህንንም ለማሳካት በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙ ወገኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ህብረተሰቡም በዚህ ላይ ጫና በማሳደር ወደ ውይይት እንዲመጡ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። አገልግሎት ሰጪዎች የሀይማኖት አባቶች ዳያስፖራዎች ምሁራን የኢትዮጵያ ህመምም ሆነ ድህነት ከባህር ወደብ ጋር የተያያዘ በመሆኑ በጋራ ቆመን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በ – አክረም ኑርያ












