የመንግሥታቱ ድርጅት በሊባኖስ ምድር የሰላም ማስከበር ተለዕኮውን በፈርንጆቹ 2027 ለማጠናቀቅ ወሰነ ።
የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት(UNSC ) በሊባኖስ ያሰፈረውን ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሁለት ዓመታት በኋላ ለማስወጣት ቀን ቆርጧል ። ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል በሊባኖስ ምድር የሰፈረው ይህ ኃይል ከቀጠናው ሲወጣ እስራኤል የበለጠ ጫና እንዳትፈጥር ስጋት ተጋርጧል።
በሊባኖስ የመንግስታቱ ድርጅት ጊዚያዊ ኃይል (ዩኒፍል) ተልዕኮውን ሲያቆም በቤይሩት እና ቴል አቪቭ መካከል አዲስ ውጥተት ሊነግስ ይችላል ተብሏል ። አንድ የመጨረሻ ዙር ጊዜ የተሰጠው ይህ ኃይል፣ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 31 -2026 ድረስ ሲዘልቅ በርካታ የቤት ስራዎችን ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።
ይህን ውሳኔ እስራኤል በበጎ ከመመልከት ባሻገር ዩኒፍል ከሊባኖስ ነቅሎ እንዲወጣ ግፊት ስታደርግ ነበር። የሰላም አስከባሪ ኃይሉ ከቀናጠው እንዲወጣ እስራኤል እጅግ የበረታ የውትወታ (ሎቢይንግ) ስራ ላይ ሰንብታለች።
በመንግስታቱ ድርጅት የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን “ላስታውሳችሁ የምፈልገው :-ከ47 ዓመታት በፊት የጸጥታው ምክር ቤት ቀጠናውን ለማረጋጋት ዩኒፍልን ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ ልኮ ነበር። ሁላችንም እንደምናውቀው ደግሞ አልተሳካለትም። ሄዝቦላህ አካባቢውን ያዘ።” በሚል ደስታቸውን ከተልዕኮው አለመሳካት ጋር አዳምረው ገልጸዋል።
የሊባኖስ መንግስት አካባቢውን መያዝ ይገባዋል እንጂ ሄዝቦላህ አሊያም ሌላ ሀይል መሆን የለበትም ሲሉም ሀሳባቸውን አጋርተዋል አምባሳደሩ። 10,800 የሚሆኑ ወታደሮች በደቡባዊ ሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል።
ታዲያ እስራኤል ውሳኔውን ስታደንቅ እና በበጎ ስትመለከተው በሊባኖስ መንግስት በኩል ግን ግራ የተጋባ ስሜት ተንፀባርቋል ።
ዘገባው የ ዘ ኒውዮርክ ታይምስ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












