አትዩ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን እና የሶስት ዓመት መሪ የእድገት ስትራቴጂ ማጠቃለያ ሪፖርትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የኢትዩ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ ኢትዩ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት እና በሶስት ዓመት መሪ የእድገት ስትራቴጂ፥ ዲጂታል ኢትዩጵያን እውን ለማድረግና የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ለመጨመር በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን አብራርተዋል።
በበጀት ዓመቱ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች የተከናወኑበት መሆኑን ገልጸው፥ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ 280 ሳይቶችን መልሶ በመጠገን ወደ አገልግሎት ማስገባት መቻሉን ገልጸዋል።
በዚህም ባተጠናቀቀው በጀት ዓመትና በስትራቴጂ ዘመኑ 1ሺ 151 ሳይቶችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት መመለስ መቻሉን ተናግረዋል። ኩባንያው በበጀት ዓመቱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማስፋት፥ 1ሺ 683 አዲስ የሞባየል ጣቢያዎችን ገንብቶ ወደስራ ያስገባበት መሆኑም ተገልጿል።
የ5G ተጠቃሚ ከተሞችን በተመለከተ በበጀት አመቱ 16 ከተሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፥ ይህም በአጠቃላይ የ5G ተጠቃሚ ከተሞችን ቁጥር ወደ 26 ከፍ ማድረጉን ዋና ስራ አሰፈጻሚዋ ገልጸዋል።
በተጨማሪም 512 ከተሞችን የ4G ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን እና ይህም አጠቃላይ የተደራሽነት ስራውን 936 ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል። ከዘህ በፊት በኔትወርክ ተጠቃሚ ያልነበሩ 459 ወረዳዎችን በኔትወርክ መስተሳሰር መቻሉንም ገልጸዋል።
ከዚህ ባሻገር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተቋሙ ላይ የተቃጡ 462 የሳይበር ሙከራዎች መክሸፋቸውን አስታውቋል።
በ- ሰላማዊት ወንድወሰን












