የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2024 በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ምንም ዓይነት ክትባት እንዳልተቀበሉ አስታወቀ።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጤና ባለስልጣናት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በመላው ዓለም ባለፈው የአውሮፓውያኑ 2024 ዘመን አንድም ክትባት ሳይከተቡ የቀሩ ናቸው ያላቸውን አስራ አራት ሚሊዮን ህጻናት አሉ ሲል ምሬቱን ገልጿል።
መረጃውን ያወጡት ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ተቋም ዩኒሴፍ ናቸው።
ዘገባው የኮሪያ ሄራልድ ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












