የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 41ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በ2018 በጀት ዙሪያ በጥልቀት እየተወያየ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት በበጀቱ ዙሪያ ጥያቄዎች ለገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ አቅርበዋል።
ለጥያቄዎቹ በማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሩ 2017 በጀት አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ከብሔራዊ ባንክ ብድር ሳንወስድ ያጠናቀቅንበት አመት ነው ብለዋል። በ 2017 በጀት አመት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ አዲስ የገንዘብ ፈንድ ፖሊሲ የወጣበት እና ወደ ተግባር የተገባበት መሆኑን አስታውሰዋል።
በመሆኑም አዲሱ የገንዘብ ፈንድ ፖሊሲ መተግበርን ተከትሎ አዳዲስ የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ከብሔራዊ ባንክ ብድር እንደማይወሰድ ተናግረው ያለው አማራጭ የመንግስት ወጪዎችን በሀገር ውስጥ ገቢዎች መሸፈን መሆኑን አስረድተዋል።
የእዳ ሽግሽግ በቅርቡ እንደሚፈረም የተጠቆመ ሲሆን ይህም ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የእዳ እፎይታ ይሰጣል ተብሏል።
በ– አክረም ኑርያ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












