በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በ82 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ላይ በተደረገ የልብ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
የልብ ቀዶ ህክምና ባለሞያው ዶክተር ፈቀደ አጉዋር የተመራው ቀዶጥገና፣ ለ82 ዓመቷ እናት የተሰራው የደም ቧንቧዎችን የመክፈትና የልብ በርን የመቀየር ቀዶ ህክምና የተሳካ እንደነበር ዶክተሩ ተናግረዋል።

ሁለት የተለያዩ ትልልቅ ቀዶ ህክምናዎች መሆናቸው ቀዶ ህክምናውን ከባድ አድርጎት ነበር ያሉት ዶ/ር ፈቀደ፣ በዚህም ሁለት የተለያዩ የደም ስሮች የመከፍት ስራም ተሰርቷል፡፡
ቀዶ ህክምናው በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ በመሆኑ ሪከርድ ሊደረግ ይገባል፡፡ ህከምናው ሲደረግም አንደኛውን ከእግራቸው ላይ ሌላኛውን ደግሞ ከደረት ስር ትልቅ የደም ቧንቧዎችን በመውሰድ የተሰራ ነው መሆኑን ዶክተር ፈቀደ የገለጹት፡፡
ለስምንት ሰዓታት በፈጀው የልብ ቀዶ ህክምና ባሳለፍነው አርብ ነው የተደረገው፣ ህክምና የተደረገላቸው እናትም በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውንም ኢፕድ ዘግቦታል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












