NBC Ethiopia
June 30, 2025
በኮሪደር ልማት እና በእርጅና ምክንያት በፈረሰዉ ህንፃ ምትክ ያስገነባውን ሁለገብ ህንጻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት ማስረከቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ሁለገብ ህንፃዉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በተለምዶ “መሐሙድ ሙዚቃ ቤት” በመባል የሚታወቀዉ የቤተክርስቲያኗ ይዞታ ላይ የተገነባ ህንጻ ነዉ። አስተዳደሩ በመደበው በጀት ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በዛሬዉ ዕለት የተመረቀዉ ህንፃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ መጠናቀቁን ከንቲባ አዳበች አቤቤ ተናግረዋል። መረጃው የከንቲባ ጽ/ቤት ነው።













