የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃቶች በኑክሌር ጣቢያዎቿ ላይ “ከባድ ጉዳት” እንዳደረሱ አምነዋል።
ለ12 ቀናት የዘለቀው ጦርነት ካበቃ በኋላ፣ የኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲን በመጥቀስ ጉዳቱ ቀላል አልነበረም፤ በኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል በማለት ገልጸዋል፡፡
አራግቺ እንደተናገሩት ቴህራን የተባበሩት መንግስታት የኑክሌር ሃላፊ ራፋኤል ግሮሲ ወደ አገሯ እንዲገቡ አትፈቅድም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ በኢራን ኑክሌር ጣቢያዎች ላይ የወሰደችው እርምጃ ምን ያህል ውጤታማ ነበር በሚል የአሜሪካ የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ክፍል ውዝግብ ውስጥ ገብቶል፡፡
ኑ እንወያይ ያሉት አራግቺ “አውሮፓውያን ደውለው ጦርነቱን አቁመው ወደ ዲፕሎማሲው ተመለሱ ይሉኝ ነበር እና እኔም ዲፕሎማሲያዊ ሂደት ውስጥ ነበርን በማለት አስረዳቸዋለው፡፡” ብለዋል። አራግቺ አክለው፣ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ በጣም የተወሳሰበ እና አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን ንግግሮችን በማጠናከር የኑክሌር ስምምነትን ማድረግ እንችላለን ብለዋል፡፡
“ፍላጎታቸው የእኛን የኑክሌር ጣቢያዎችን ካወደሙ በኋላ ባዶ እጃችንን በድርድር ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጥ ነበር፤ ግን ይሄ እንዲሆን አልፈቀድንም” ነው ያሉት።
በ ሔርሜላ ተመስገን












