በሜክሲኮ ጉዋናጁዋቶ ግዛት በሀይማኖት ክብረ በዓል ላይ አንድ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ ህጻናትን ጨምሮ 12 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡
ጥቃት አድራሹ እና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አካላትን በመፈለግ ላይ እንደሚገኙም የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ በኢራፑዋቶ ከተማ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ጥቃት ማድረሱን በተንቀሳቃሽ ምስል መለቀቁንም ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንቷ ክላውዲያ ሼንቡአም በጥቃቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው፣ ወንጀለኛውን በማፈላለግ ላይ መሆናቸውን ነው የገለጽት፡፡ አሁን ላይ በሜክሲኮ የተፈጠረው ሀይማኖት ጥቃት ከባለፈው ግንቦት ጀምሮ ለሁለኛ ጊዜ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስጣናት ተናግረው::
ባለፈው ግንቦት በጉዋናጁዋቶ ግዛት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመ ጥቃት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ዘዊክ መጽሄት ነው ያስነበበው፡፡
በቶማይ መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












