። ። ። ። ። ። ። ። ።
የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ጥምረት ኔቶ ዋና ጸሀፊ ማርክ ሩቴ ጋር በሮም ተገናኙ፡፡
ከሜሎኖኒ ጽህፈት ቤት የወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት፣ የስብሰባው ዋና ዓላማ በሚቀጥለው ወር በኔዘርላንድ ሄግ በሚደረገው የኔቶ አባል ሀገራት ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
ማርክ ሩቴ እና ሜሎኒ በጋራ ደህንነት ላይ ያተኮረ ውይይት በማድረግ የኔቶን የመከላከያ በጀት ለመጨመር እና ህብረቱ ራሱን የሚከላከልበትን መንገድ ለመፍጠር መክረዋል ተብሏል፡፡
ጣልያን ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት ኔቶ 1.5 በመቶ የመከላከያ ወጭ በማውጣት ዝቅተኛ ሀገር እንደሆነች ይታወቃል፡፡
ኔቶ ከህብረቱ አባል ሀገራት 2 በመቶ ለወታደራዊ ወጭ እንደሚሰበስብ የሚታወቅ ሲሆን፤ ዶናልድ ትራምፕ ከመጡ በኋላ 5 በመቶ ማውጣት አለበት ማለታቸውን ተከትሎ ህብረቱ ፈተና ውስጥ እንደሆነ ይነገራል፡፡
አናዶሉ ነው የዘገበው፡፡
በ – ቶማይ መኮንን












