:::::::::::::::::::::::::::::::::
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ባለፉት 20 ወራት ከ55 ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መሞታቸውን ተገለጸ፡፡
የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ከተጀመረበት እ.አ.አ ጥቅምት 7 2023 ጊዜ አንስቶ 55,1 መቶ4 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከ 127 ሺህ በላይ መቁሰላቸውን የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በርካቶች በፍርስራሹ ስር ወይም ህክምና ባለሙያዎች በማይደረስባቸው ቦታዎች ተቀብረው ቀርተዋል ሲል ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡ ከ 55 ሺሕ ሟቾች ውስጥም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው ተገልጻል፡፡
ማባሪያ ባጣው የእስራኤልና ሀማስ ግጭት የማቾች ቁጥር በሁለቱም ወገኖች እየጨመረ ይገኛል፡፡ በተለይም እስራኤል ሀይሎች በጋዛ ሰርጥ በተደጋጋሚ በሚያደርሱት የተቀናጀ የአየርና የምድር ጥቃት በየቀኑ በርካታ ፍሊስጤማውያንን ህይወት እያሳጠ መሆኑን ነው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












