NBC Ethiopia
ሰላም ይልማ

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የፌዴራል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ባለድርሻ አካላቱ አገርን ወደፊት ያራምዳሉ ያሏቸውን አጀንዳዎች እያቀረቡ ነው።
በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ፣ ፖለቲከኞች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የዲሞክራሲ ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት እና መሰል የፌደራል ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎችን በቡድን በመሆን አጀንዳዎች ላይ እየተመከረ ይገኛል።
የፌደራል ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰቢያ ምዕራፍ በነገው ዕለት የሚጠናቀቀ ይሆናል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












