የአርሰናሉ ተከላካይ ከፉልሃም ጋር በተደረገ የፕሪምየ ሊግ ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ መውጣቱ አይዘነጋም።
የጉዳቱ መጠን እና ምን ያህል ከሜዳ እንደሚያርቀው ባይገለጽም፣ መድፈኞቹ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ከውድድሩ ልዕለ ሃያል ሪያል ማድሪድ ጋር በሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ እንደደማይሰለፍ ተገልጿል።
ማግሃሌሽ በአርሰናል አይነኬ ከሆኑ ተጫዋቾች የሚመደብ ሲሆን፣እንደ ብዙዎች ግምት የዘንድሮው የውድድር አመት የክለቡ ምርጥ ተጫዋች ነው።
በጉዳት እስከዚህም የማይፈተነው ብራዚላዊው ከዊሊያም ሳሊባ የፈጠረው ጥምረት የክለቡን የተከላካይ መስመር አይደፈሬ አድርጎታል።
ማግሃሌሽ የቆሙ ኳሶችን በመከላከል እና በማጥቃት የሚሰጠውን ግልጋሎት የሚያጣው አርሰናል በስፍራው ያኩብ ኪቪዮርን እንደሚያሰልፍ ይጠበቃል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ” በጉዳት መፈተናችን መፍትሄ እንድንፈልግ ያደርገናል” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












