፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስድስተኛ ዙር ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች ስልጠናን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አስጀምሯል።ስልጠናው ለቀጣይ 4 ወራት በሲቪል ሰርቪስ ዩቨርሲቲ እንደሚሰጥም ተገልጿል። ሰልጣኞች በቆይታቸው የፖሊሲ፣ የአካዳሚክ እና ተግባር ተኮር ስልጠናዎች እንደሚወስዱ ተመላክቷል።

ስልጠናው ከዚህ ቀደም ለአምስት ዙሮች የተሰጠ ሲሆን በስድስተኛው ዙር 50 ሰልጣኞች የሚሰለጥኖ ሲሆን በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሰልጣኝ ዲፕሎማቶች መገኝታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።












