፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 03 2017| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ምግብ መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከባህላዊ ህክምና እና አንዳንድ ዘመናዊ ህክምና የተያያዙ ጎጂ የጤና ማስታወቂያዎች መበራከታቸው ገልጿል።

የጤና ማስታወቂያዎቹ አሳሳች በሆነ መልኩ፣ ማህበራዊ እሴትና ባህልን ባላከበረ ሁኔታ ፣ ፍቃድ ሳይሰጣቸው እንዲሁም ህግና ስነ-ምግባርን ባላከበረ መልኩ እንደሚሰራጩ ተነግሯል።
የጤና ተቋማት ከተሰጣቸው የሞያ ማረጋገጫ ደረጃ በላይ አገልግሎት እንደሚሰጡ በማድረግ፣ የሞያ ስነምግባርን በሚጥስ አኳኋን የታካሚን የውስጥ አካል በማሳየት፣ በጎጂና ኋላቀር የተፈረጁ በባህላዊ ትርጓሜ ማዕቀፍ የማይታዩ የጥንቆላ መልዕክቶች ጭምር በመጣስ ማስታወቂያዎቹ ይሰራጫሉ ሲል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድና ግንዛቤ ለመስጠት ያለመመ የፖናል ውይይት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












