፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 23 2017| NBC ETHIOPIA- ሩሲያ ከሁለት አመታት ብርቱ ጦርነት በኋላ በዩክሬን ቁልፍ የተባለችዋን ከተማ በእጇ ማስገባቷ ተሰምቷል ፤ አሁን በሩሲያ ጦር ሀይል እጅ የገባችው የዩክሬኗ ከተማ ቩህለዳር ትባላለች።
የዩክሬን ጦር ሀይል ከተማዋን በሩሲያ ላለማስነጠቅ በጥርሱና በጥፍሩ ለሁለት አመታት መዋጋቱም ነው የሚነገረው ፤ ይሁንና የሩሲያ ጦር ሀይል በበላይነት ከተማዋን ቀምቶ መቆጣጠሩን ከዚያው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

የቩህለዳር ከተማ በሩሲያ ጦር ሀይል እጅ መግባት ለክሬምሊን ታላቅ ድል ሲሆን ለዩክሬን ደግሞ ከምዕራባውያኑ እንደገና የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንድትማጸን ያደርጋታል ነው የተባለው ዘገባው የ ኤ ቢሲ ኒውስ ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv


See insights
Boost a post
Like
Comment
Send
Share












