፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 22 2017| NBC ETHIOPIA-“ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ቅዳሜ በሆራ ፊንፊኔ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፣ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ገልጸዋል ።
ኢትዮጵያ ካላት በርካታ የአደባባይ በዓላት መከከል አንዱ የሆነው ኢሬቻ ማህበራዊ ትስስርን በመፍጠሩ ረገድ የጎላ አስተዋጽዖ እንዳለው ተናግረዋል ።
በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ ከተሞች ወደ መዲናዋ የሚገቡ በርካታ ሰዎች በመኖራቸው መሰረታዊ የሆነውን የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ያሳድጋል ነው ያሉት ።
በዓሉ እራሱን ችሎ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት ፣ ሳይንስና የባህል ድርጅት ላይ እንዲመዘገብ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል።
በ-የአብስራ ብርሃኑ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












