፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 21 2017| NBC ETHIOPIA- በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩና ይኖሩ የነበሩ ዲያስፖራዎች አጀንዳቸውን ለሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።
ከአዲስ አበባ ዲያስፖራዎች ማህበር አጀንዳውን የተረከቡት የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ተጉዞ ከኢትዮጵያውያን ጋር ሲመካከር መቆየቱን ገልፀው ዲያስፖራው አለኝ የሚለውን ዓጀንዳ ለመቀበል ኮሚሽኑ ሁሌም በሩ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።

ማህበሩ በበኩሉ ምክክሩ ካለው ጉልህ ፋይዳ አንፃር በሚፈለገው ሁሉ ከኮሚሽኑ ጎን እንደሚቆም ቃል ገብቷል።

የአዲስ አበባ ዲያስፖራዎች ማህበር በፕሬዝዳንቱ አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ አማካኝነት ቀደም ሲል ስለምክክሩ ለሰራው ሙዚቃ የቪዲዮ ክሊፕ ሰርቶ ለኮሚሽኑ አስረክቧል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












