Wednesday, November 18, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Environment

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026
in Environment
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ኢትዮጵያ ለኮፕ 32 አዘጋጅነት እንድትመረጥ ባደረጓት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እና የአካባቢ ጥበቃ ስኬት ከተባበሩት መንግስታት ድረጅት ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና ኢኮኖሚዋን ለአረንጓዴ ልማት ምቹ ለማድረግ የምታከናውነው ተግባራዊ ስራ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻሉን የኮፕ 32 ፕሬዝዳንሲ ቡድን አባል እና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር አስተባባሪ ዶክተር አደፍርስ ወርቁ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት ዶክተር አደፍርስ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚወጡ የኢኮኖሚ፣ የጤና እና የኢነርጂ ፖሊሲዎች ሁሉ ቀዳሚውና ዋነኛው የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ መሆኑን አስረድተዋል።

ማንኛውም የልማት ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆነው መሬት ላይ እስከሆነ ድረስ፣ የአየር ንብረቱ ከተዛባ፣ መሬት ከተጎሳቆለና ውሃ ከተበከለ የሁሉንም ዘርፎች ስርዓት ስለሚያናጋ ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት መስጠት የግድ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ የካርበን ልቀትን በመቀነስና ኢኮኖሚዋን አረንጓዴ በማድረግ ረገድ የሄደችበት ርቀት በአካባቢ ጥበቃው ዘርፍ ዓለም አቀፍ ማሳያ እንድትሆን አድርጓታል ያሉት ዶክተር አደፍርስ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ይህንን ስኬት በተጨባጭ ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለአብነትም ባለፈው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ብቻ ከ26 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነቂስ ወጥተው በመሳተፍ በአንድ ጀምበር  805 ሚሊዮን ችግኞችን መትከላቸውን ነው ያስታወሱት።

ይህ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ አፈርንና ውሃን ከመጠበቅ ባለፈ ሀገሪቱ ከካርበን ንግድ ተጠቃሚ እንድትሆን መሰረት የሚጥል ትልቅ ሀገራዊ አቅም መሆኑ ተመላክቷል።

ሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲዎችን ከማውጣት ባለፈ መሬት ላይ አውርዳ በተግባር በማረጋገጧ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተግባሪ ሞዴል ሀገር በመባል እውቅና ማግኘቷን አስተባባሪው አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የ32ኛውን የሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንድታዘጋጅ መመረጧም የዚሁ ዓለም አቀፍ እውቅናና የመሪነት ሚናዋ አንዱ አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን የኮፕ 32 ፕሬዝዳንሲ ቡድን አባል የሆኑት ዶክተር አደፍርስ አንስተዋል።

የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማትና የካርበን ቅነሳ ስኬት ዘላቂ ለማድረግ የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያለውን እያንዳንዱን የህብረተሰብ ክፍል በማነሳሳት በአረንጓዴ አሻራና በአፈር ጥበቃ ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ይህ ቀጣይነት ያለው ጥረት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ከመጠበቅ ባለፈ ለኮፕ 32 ጉባኤ የምታቀርበውን ተሞክሮ ይበልጥ የሚያጎላ እና ከአረንጓዴ ኢኮኖሚው የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያረጋግጥ ይሆናል ብለዋል።

በ ታደለ ገበየሁ

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: climatechangeCOP32EthiopiaGreen Legacyአረንጓዴ አሻራ
ShareTweetShare
Previous Post

“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

Next Post

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

Related Posts

No Content Available
Next Post
ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026
“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

November 18, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

በተመድ እውቅና ያገኘው አረንጓዴ አሻራ!

November 18, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?