Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በሀገሪቱ የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና ውጤታማነትና ለተግባራዊ እውቀት ሽግግር ትልቅ ዕድል ፈጥረዋል

በሀገሪቱ የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና ውጤታማነትና ለተግባራዊ እውቀት ሽግግር ትልቅ ዕድል ፈጥረዋል

October 26, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

በሀገሪቱ የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና ውጤታማነትና ለተግባራዊ እውቀት ሽግግር ትልቅ ዕድል መፍጠራቸውን የኢትዮጵያ የቴክኒክ ልህቀት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ የቴክኒክ ልህቀት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የተተገበሩት የስልጠና ፕሮግራሞች ለክህሎት ማደግ ከፍተኛ ትኩረት የሰጡና የወጣቶችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ናቸው።

ይህም የገበያውን ክፍተት የሚሞሉ አዳዲስ የሙያ ዘርፎችን በማካተት ለቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ውጤታማነት አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል።

ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ዘመኑን እና ቴክኖሎጂውን ፍላጎት ለማሟላት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ ሮቦቲክስ፣ ባዮሜዲካል እና የኒው ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ዘመኑን የዋጁ አጫጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ሰልጣኞች ከተቋሙ ከሚያገኙት ተግባር ተኮር ትምህርት ባለፈ በኢንዱስትሪዎች ያለውን ጠቃሚ ተሞክሮ እንዲቀስሙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ ስራ እየተከናወነ ነው።

ተቋሙ ከ170 በላይ ልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመፈራረም በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአውቶሞቲቭ፣ በቱሪዝም እና በማዕድን ዘርፎች በክህሎትና በእውቀት የዳበረ የሰው ሃይል ለማፍራት በቅርበት እየሰራ ይገኛል።

በተጨማሪም የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን ኢንስቲትዩቱ ችግር ፈቺ የሆኑ የቴክኖሎጂና የምርምር ውጤቶች የሚሰሩበት ምህዳር ለመፍጠር “ስኪል ኢትዮጵያ” በሚል ኢንሼቲቭ እየተንቀሳቀሰ መቆየቱን ተናግረዋል።

የሀገሪቱን ልማት ለማፋጠን “ስኪል ኢትዮጵያ” የተሰኘው ኢንሼቲቭ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂና የምርምር ውጤቶች የሚፈጠሩበት ምህዳር በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።

ኢንሼቲቩ የፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ሰልጣኞች በመደገፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በግብርና፣ በአይሲቲ እና በማዕድን ዘርፎች 99 የሚደርሱ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማስገኘቱን አንስተዋል።

እንደ ማሳያነት በግብርናው ዘርፍ ከተጠቀሱት ቴክኖሎጂዎች በተጨማሪ የገጠር ኮሪደር ልማትን ለማፋጠን የሚያግዙ የብሪክስ ማኑዋል እና የሀይድሮሊክ ማሽኖች በብዛት ተመርተው ለክልሎች ተደራሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የስልጠና ማዕከላት ውጤታማነት ለማጎልበት የአካባቢን ጸጋና አቅም መሰረት ያደረጉ ፕሮግራሞች እየተከፈቱ መሆኑ ገልጸዋል።

በሀገሪቱ የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚኙም ነው የገለጹት።

ኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በማፋጠን ረገድ የቴክኒክና ሙያ መስኩ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ዘርፉን የበለጠ ለማጠናከር በሀገር ውስጥ መተካት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን የመፍጠር ስራዎች ላይ ትኩረት መደረጉንም ተናግረዋል።

በዚህም በየደረጃው ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን በማፍራት የሀገሪቱን የልማት ጉዞ የማፋጠን ድርሻውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ምንጭ፡ኢዜአ

Source: @NBCETHIOPIA ​
Via: @NBCETHIOPIA ​
Tags: #addisababaEthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ምዕራፍ እያበሰረች ነው ተባለ !

Next Post

የግብፅ የውጭ ፖሊሲ ተቃርኖና የቱርክ ተፅዕኖ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የግብፅ የውጭ ፖሊሲ ተቃርኖና የቱርክ ተፅዕኖ

የግብፅ የውጭ ፖሊሲ ተቃርኖና የቱርክ ተፅዕኖ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞዛምቢክ ናካላ ከተማ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞዛምቢክ ናካላ ከተማ በረራ ጀመረ

“የድል ሰራዊት” – 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን

“የድል ሰራዊት” - 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?