
ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ብርሀናት (አውሮራ) በምድር ከፍተኛ ኬክሮስ አካባቢዎች አስደናቂ ትርኢት አሳይተዋል።
የሰሜን ብርሀናት (አውሮራ ቦሪያሊስ) በሰሜን አሜሪካ እና በሰሜናዊ አውሮፓ ክፍሎች፣ እንዲሁም በጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ስዊትዘርላንድ ክፍሎች ታይተዋል። የደቡብ ብርሀናት (አውሮራ አውስትራሊስ) ደግሞ በደቡብ እና ምዕራብ አውስትራሊያ እንዲሁም በኒውዚላንድ ታይተዋል።

እነዚህ ተለዋዋጭ ቀለም ያላቸው የብርሃን ትርኢቶች የፀሐይ ንፋስ ከምድር መግነጢሳዊ መስክ ጋር ካለው መስተጋብር የሚመጡ የጠፈር የአየር ንብረት መገለጫ ምልክቶች ናቸው።
አውሮራዎች የሚከሰቱት ከፀሐይ የሚመጡ ኃይል የተሞሉ ቅንጣቶች በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ከሚገኙ ጋዞች ጋር ሲገናኙ ነው። የምድር መግነጢሳዊ መስክ እነዚህን ቅንጣቶች ወደምድር ሰሜን እና ደቡብ ዋልታዎች ይመራቸዋል፤ በዚያም ከኦክስጅን እና ከናይትሮጅን ጋዝ ቅንጣቶች ጋር በመጋጨት የሚፈጥሩት ኃይል ባለቀለም ብርሃን ሆኖ ይታያል።
አውሮራዎች በምድር መግነጢሳዊ ዋልታዎች ዙሪያ በሁለት ኦቫሎች የሚታዩ ሲሆን ለሚቀጥሉት ጥቂት ወራት መታይየታቸውን ይቀጥላሉ።
በ- ዳንኤል መኮንን











