ፈተናውን 5መቶ 63ሺህ 5መቶ 1 ተማሪዎች ይወስዳሉ

በ6ዙር የሚሰጠውን የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂ ፈተና በመጀመሪያው 3ዙር የሚሰጠውን ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ዛሬ መውሰድ ጀምረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕሮፌሰር) ፈተናውን አጠቃላይ 5መቶ 63ሺህ 5መቶ 1 ተማሪዎች ይወስዳሉ ብለዋል።
ከእነዚህ ውስጥም 3መቶ 6ሺህ 4መቶ 56 የተፈጥሮ እና 2መቶ57ሺህ 45 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።
ፈተናው በመላው ሀገሪቱ ትግራይን ጨምሮ ለሚገኙ ተማሪዎች በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕሮፌሰር ) አስታውቀዋል።
ፈተናው በበይነ መረብና በወረቀት እስከ ሐምሌ 16 ፣2018 መሰጠቱንም ይቀጥላል።
የወረቀት ተፈታኞች ከሐምሌ 1ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀምርም ተገልጿል።
በ-እየሩሳሌም ዓለሙ












