
መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ 10 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናነት (Special Economic Zones – SEZs) አሳድጓል። እነዚህም ፓርኮች፦
1 አዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
2 ባህር ዳር ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
3 ቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
4 ደብረ ብርሃን ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
5 ሀዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
6 ጂማ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
7 ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
8 ኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና፣
9 መቐለ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና እና
10 ሰመራ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና ናቸው።
የልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች መመስረት ባለሀብቶች ሰፋ ያለ የታክስና የቀረጥ ማበረታቻ እንዲያገኙ፣ የንግድ ስርአቱ እንዲቀላጠፍና የሎጂስቲክስ ወጪ እንዲቀንስ ያደርጋል።
በአጠቃላይ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በዘርፍ ተለይተው የተደራጁ በመሆናቸው ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለምርታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።
እነዚህ ፓርኮች የውጭ ኢንቨስትመንትን (FDI) በመሳብ ረገድም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ ከቻይና፣ ህንድ፣ ሳዑዲ አረቢያና ቱርክ የመጡ ግዙፍ ኩባንያዎች በፓርኮቹ ውስጥ በመሰማራት የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፋጠን አድርገዋል።
በተለይም የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የቆሻሻ ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል (Zero Liquid Discharge) ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይቷል።












