
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንትና የጸረ አፖርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በሰለጠኑበት ኮልፌ ፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ የተሰየመው የመታሰቢያ ሙዚየም ተመርቋል።
በምረቃ መርሃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኖንሴባ ሎሲ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ፖሊስ ምስረታ 117 ዓመታትን ያስቆጠረ ከአፍሪካ ቀዳሚው ተቋም ነው።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ የነፃነት ትግል የጎላ አበርክቶ እንዳለው ገልጸው፤ የዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አባት የሆኑትን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ አሰልጥኗል ብለዋል።
ኔልሰን ማንዴላ የፀረ አፓርታይድ ትግልን ለመቀላቀል እኤአ በ1962 በኢትዮጵያ ለወራት ስልጠና መውሰዳቸው ይታወቃል።
Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
NBC ETHIOPIA












