February 24, 2026
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሶስት ዋና ዋና በተባሉ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በርካታ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 16ተኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያዘጋጁ እድሉ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም ፍላጎት ካሳዩ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ እና በበርካታ መስፈርቶች ድጋፍ አግኝታ መመረጧን ገልፀዋል። ለመመረጥ እንደ ምክንያት ከጠቀሱዋቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት አምስት አመታት በሰበዓዊ መብት አያያዝ ያሳያየው አበረታች ስራዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉባዔውን ኢትዮጵያ ማካሄዷ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ያሳየችውን መልካም አፈፃፀም እውቅና የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ አህጉራዊያና አለም ዓቀፍ ስብሰባዎች የማባካሄድ ልምዶች ይበልጥ የሚገኝበት ነው ብለዋል። ጉባዔውን ለማካሄድ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሏቸው አካላት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው በሀገራዊ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና ግኝቶች ዙሪያ እና የባለፉት አንድ አመት የኮሚሽኑ የስራ ክንውን ግምገማ ውጤት ይፋ አድርገዋል።
በ- ኢየሩሳሌም ዓለሙ












