የተለያዩ አገራት አዲሱን 2026 ዓመት ተቀብለው በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡

በዓለም ዙሪያ 2026 ሲገባ በተለያዩ ርችቶች እና እንደየአገራቱ ባህል አህጉራት በደማቁ ተቀብለውታል ፡፡
እንደሰዓት አቆጣጠር ስልታቸው እና እንደሚገኙበት ቦታ አገራት አዲሱን ዓመታቸውን ሲቀበሉ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች አጅበው ነው፡፡
የፓስፊክ ደሴቷ ኪሪባቲ ቅድሚያ አዲሱን 2026 ስትቀበል ፣ሳማዖ ፣ቶንጋ እና ኒው ዚላንድም አዲሱን ዓመት ግንባር ቀደም ከተቀበሉ አገራት መካከል ናቸው፡፡
እነኪሪባቲ 2025ን በመሰናበት የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የአሜሪካዎቹ አላስካና ሃዋኢ ደግሞ 2025ን በመሰናባት የመጨረሻዎቹ ይሆናሉ፡፡
ኒው ዚላንድ 2026ን በመቀበል ከመጀመሪያዎቹ መካከል ከመሆኗም ባሻገር ርችት በመተኮስ በደማቁ አክብራዋለች፡፡
ከኒው ዚላንድ ባሸገር አውስትራሊያ ደማቁን የአዲስ ዓመት አከባበር በአደባባይ ለዓለም አሳይታለች፡፡
በሲዲኒ ሃርበር ድልድይ ዓለም የምትጠብቀውን ደማቁን የርችት ስነ ስርዓትም አድርጋለች ፡፡
ጃፓን፣አሜሪካ፣ቻይና ፣ብራዚል፣ደቡብ ኮሪያ ፣ዩናትድ አረብ ኤሚሬቶች እና ሌሎች በርካታ አገራት 2026ን ከተቀበሉት መካከል ናቸው ፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












