NBC Ethiopia
December 13, 2025
ኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ የኢራናዊቷ የኖቤል ተሸላሚ ናርጅስ መሐመዲ እስርን “አሰቃቂ” ሲል አወገዘ።

የ2023 የኖቤል ተሸላሚ የሆነችው እና በእስር ላይ ከርማ የተፈታችው ኢራናዊቷ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ናርጅስ መሐመዲ፥ በኢራን በቁጥጥር ስር መዋሏን የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ በትላንትናው እለት አስታውቋል። ናርጌስ በኢራን በሚገኘው ኤቪን በሚባለው ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደምትገኝም ኮሚቴው አስታውቋል።
የሰብአዊ መብት አቀንቃኝ እና የነፃነት ታጋይ በመሆን በሀገሯ ስሟ በጉልህ የሚጠቀሰው ናርጌስ፥ ሽልማቱ የተበረከተላት በኢራን ሰብአዊ መብት፣ ነፃነት እና ዴሞክራሲ እንዲከበር ባደረገችው ተጋድሎ ነው። ወጣቷ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና እንዲቆም ያደረገችው ተግባራትም በኖቤል ኮሚቴ ጭምር ሙገሳን አስገኝቷቷል።

ይሁንና ናርጅስ ቀደም ሲል በእስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ፕሮፓጋንዳ አሰራጭተሻል በሚል ክስ ተመስርቶባት ፤የቅጣት ውሳኔዎችንም ተቀብላ በእስር ላይ ቆይታለች። ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይም ከቴህራን ኢቪን እስር ቤት ተፈትታ ነበር።

የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴ ትላንት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ፥ናርጅስ በኢራን በቁጥጥር ስር መዋሏን ጠቅሶ፥ የኢራን ባለስልጣናት ያለችበትን ቦታ በአስቸኳይ እንዲገልጹ፣ ደህንነቷን እንዲያረጋግጡ እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ ሲል ጠይቋል። እስሩ የተፈጸመው የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ተሸላሚ የሆነችው ቬንዙዌላዊቷ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ሽልማቷን ለመቀበል ኖርዌይ ከገባች አንድ ቀን በኋላ ነው ሲል የበገበው ሮይተርስ ነው።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን












