December 8, 2025
ታይላንድ በካምቦዲያ ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች። በካምቦዲያና ታይላንድ መካከል በአዲሰ መልክ የተኩሰ ልዉዉጥ መደረጉ ኤዠያ እንዳይረጋጋ ያደርጋል የሚል መረጃ በመጋራት ላይ ይገኛል።

የፕሬዚዳንት ዶናልደ ትራምፕ የዕርቅ ሰምምነት ፊርማ መጣሱንም ያረጋግጣል። በአዲሰ መልክ ባገረሸዉ ዉጥረት አንድ የታይላንድ ወታደር ህይወቱን ሲያጣ አራቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ሁለቱ ወገኖች ጦርነቱን በመቀሰቀሱ ረገድ ርሰበርሰ እየተካሰሱ ቢገኙም ደቡብ ምስራቅ ኤዠያን ከባድ ወጥረት ዉሰጥ ከተዉ በሚል በቀጠናዉ አገራት እየተተቹ ነዉ። የካምቦዲያ መንግስት ጥቃቱ ቀድሞ ተሰንዝሮብኛል ቢልም ካምቦዲያ አፀፋዊ ምላሽ ነው የሰጠሁት በሚል ትከሳለች።

ሐምሌ ላይ አገራቱ ለአምሰት ቀናት ያህል ሲዋጉ 48 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እና 300,000 የሚሆኑት መፈናቀላቸዉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም በማሌዠያዉ ፕሬዚዳንት አንዋር ኢብራሒምና በዶናልድ ትራምፕ አማካኝነት የሰላም ስምምነት ካምቦዲያና ታይላንድ ተፈራረመዉ ነበር።
ዘገባዉ የቢቢሲና አልጀዚራ ነዉ :: በ-ቢኒያም ካሴ












