NBC Ethiopia
December 6, 2025
በአሜሪካ ቨርጂኒያ የሚገኝ የመጠጥ መደብር ወስጥ “ራኩን” የተባለ እንስሳ ሱቁን ሰብሮ በመግባት በርካታ ጠርሙሶችን ከመደርደርያ በማውረድ ጠጥቶ ራሱን ስቶ ተገኝቷል። ራኩን ከታችኛው መደርደሪያ ላይ ያሉ ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን ጠርሙሶች ሰባብብሮ ከጠጣ በኋላ፣ በመፀዳጃው ቤት ውስጥ ወድቆ ራሱን ስቶ ነበር።

እንስሳው በተለይም የመረጠው የመጠጥ ዓይነት ደግሞ “ስኮች” የተባለውን ውስኪ እንደነበር ተገልጿል። መደብሩ በአሜሪካ ለሚከበረው የምስጋና ቀን (Thanksgiving) ተዘግቶ በነበረበት ወቅት ነው ይህ አጋጣሚ የተከሰተው።
ሰራተኞቹ በማግስቱ ወደስራ ሲገቡ የተሰበሩ ጠርሙሶች እና መሬት ላይ የፈሰሰ መጠጥ እና ሰክሮ የተዘረረውን እንስሳ አግኝተውታል።

የእንስሳት ቁጥጥር ኃላፊ የሆኑት ማርቲን ስለ ጉዳዩ ሲያብራሩ፣ እንስሳው ከጣሪያው ንጣፎች በአንዱ በኩል ሾልኮ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ እንደልቡ ጠርሙስ እየሰበረ ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ከአቅሙ በላይ በመስከሩ ሽንት ቤት ሄዶ በመተኛት ቀሪዎቹን ሰዓታት አሳልፏል ብለዋል።

ይህንን ክስተት የሚያሳየው ቪዲዮ ጥራት የሌለው በመሆኑ፣ ራኩኑ በሽንት ቤት ውስጥ ራሱን ከመሳቱ በፊት ምን ያህል አልኮል እንደጠጣ በትክክል አልታወቀም ተብሏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ዳንኤል መኮንን












