
ቱርክ ውስጥ የሚገኙ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው የዱር ፍየሎች ከሙሉ ጨረቃ ብርሃን ፊት በመቆም አስደናቂ ትዕይንት በመፍጠር የጎብኚዎችን ቀልብ መሳብ ችለዋል።
በቱርክ ሰማይ ላይ የታየችው እና ከሌላው ጊዜ የበለጠ ግዝፈት የነበራት ሙሉ ጨረቃ በዓለም ዙርያ አስደናቂ ትዕይንቶችን ፈጥራለች።
ቱርክ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸው የዱር ፍየሎች፣ እየወጣች ካለችው ጨረቃ ፊት በተራራ ሸንተረር ላይ ቆመው በመታየት ተጨማሪ ድምቀት ሆነዋል።

ቁልቁለታማ በሆኑ ዓለታማ ስፍራዎች የሚኖሩት እነዚህ ፍየሎች፣ የግጦሽ ሳር ለመመገብ በቡድን ሆነው በረዶ ወደሚቀንስባቸው የግጦሽ መስኮች የሚወርዱ ሲሆን ጨለማ ሲወርድ፣ ከአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና ከአዳኞች መጠለያ ለመፈለግ ወደ ተራራማ መኖሪያዎቻቸው ይመለሳሉ።
የዱር ፍየሎች ከተራራው ሸንተረር ጀርባ የምትወጣው ሙሉ ጨረቃ ፊት ላይ ሆነው ላይ መታየታቸው ማራኪ እይታ ፈጥሯል።
እነዚህ በአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት (IUCN) ሊጠፉ የተቃረቡ ዝርያዎች ቀይ መዝገብ ውስጥ የተዘረዘሩት የዱር ፍየሎች፣ 2,500 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኘው ፓጋን ተራራ (Pagan Mountain) ላይ ነው የታዩት።
በ-ዳንኤል መኮንን












