የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት በሀገሪቱ ረዥሙን የመንግስት መዘጋት እንዲያበቃ የሚያስችል ድምፅ ሰጠ፤ 43 ቀናትን ያስቆጠረው የመንግስት መዘጋት በአሜሪካ ታሪክ ረዥሙ ሆኖ ተመዝግቧል፤ በሀገሪቱ የመንግስት መዘጋትን ተከትሎ በየዘርፉ በርካታ ፈተናዎች ገጥመዋል፤
ለአብነትም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ያለ ክፍያ ሲሰሩ ቆይተዋል፣ ተባረዋል፣ 43 ሚሊዮን ከመንግስት የምግብ ድጎማን ያገኙ የነበሩ ዜጎች እርዳታ ተጓቷል፣ የጤና መድህን ላይ ሰፊ ቀውስ ውስጥ ከቷል፤
እንዲሁም የአቬሽን ኢንደስትሪውን ሰራተኞች ቅነሳ፣ በረራዎች መሰረዝና መስተጓጐል በማስከተል የሀገሪቱን የአቬሽን ዘርፍ ከፍተኛ ውዝግብና ኪሳራ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል፤ በዚሁ ምክንያት ከ1 ሺ 200 በላይ በረራዎች እንዲሰረዙ ምክንያት ሆኗል፤
ያለፈው ሰኞ ይህ ቀላል የማይባል ቀውስን ያስከተለው የመንግስት መዘጋት እንዲያበቃ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ በማርቀቅ የአሜሪካ ሴኔት ለምክር ቤት ልኳል፤ ምክርቤቱ በበኩሉ በረቂቁ ላይ ተወያይቶ በ222 እሺታና በ206 እምቢታ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ ውሳኔ እና ፊርማ ያገኝ ዘንድ አሳልፏል፤
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሰአት በኋላ በነጩ ቤተመንግስት የመንግስት መዘጋት ማብቂያ ፊርማቸው ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ይህም ረዥሙ የቅዠት ቀን ማብቂያ ይሆናል በማለት በርካቶች ተስፉን ጥለውበታል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












