ቬንዙዌላ ”ለአሜሪካ ጥቃት ”ራሷን እያዘጋጀች መሆኑን አሳወቀች።
ቬንዙዌላ በርከት ያለ ኃይሏን በማንቀሳቀስ የአሜሪካን ጥቃት ለመመከት ዝግጅት ላይ እንደሆነች ታውቋል። በላቲን አሜሪካ የዋሽንግተን ግዙፍ የጦር መርከቦች መንቀሳቀሳቸው ለካራካስ ስጋት ሆኖባታል።
የትራምፕ አስተዳደር የኒኮላስ ማድሮን መንግስት ለመገልበጥ ውጥኑ አለው በሚልም ቬንዙዌላ ትወነጅላለች። ጦር የማንቀሳቀስ ዝግጅቱም የባህር፣ የአየር የምድር እና የሚሳዔል ኃይሉን የሚያካትት ነው ተብሏል።
ፖሊስ፣ ሚሊሺያዎች እና በጥቅሉ ዜጎችም የዚሁ አካል ናቸው ስትል ካራካስ አሳስባለች። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የማዱሮ መንግስት አደንዛዥ ዕጽ ወደ አሜሪካ ምድር እንዲገባ በማድረግ ወንጀል እየሰራ ነው የሚል ክስ ያቀርባሉ።
ምንም እንኳን ዶናልድ ትራምፕ ካራካስ ላይ ጦር የማዝመት ዕቅዱ የለኝም ቢሉም በካርቢያን ባህርና በፓስፊክ ውቅያኖስ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ወታደር የማዝመት ያህል ሆኗል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












