እስራኤል አምስት ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቀቀች።
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል እየተተገበረ ባለው የሰላም ስምምነት መሰረት አምስት ፍልስጤማውያን ከእስር መፈታታቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል።
ባሳለፈው ወር በሀማስና በእስራኤል መካከል ያለው ግጭት እልባት ያገኝ ዘንድ በሁለቱ ወገኖች የሰላም ስምምነት መደረሱ ይታወሳል ። በዚህም እስራኤል በርካታ ታጋዮች መልቀቋ ሲታወስ ስምምነቱ መተግበር ከጀመረ በኃላም አምስት እስረኞችን መልቀቋ ነው የተሰማው።
ሰኞ ምሽት የተፈቱት እነዚህ እስረኞች ለህክምና ወደ አል-አቅሳ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ነው የተገለጸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን አሁንም በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በአፋጣኝ ከእስር እንዲፈቱም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አሳስበዋል ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ- ሰላማዊት ወልደገሪማ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












